ዛሬም ቅዱሳን አባቶች ከኢትዮጵያ ተሰወሩ የተሰወሩበት ገዳምና ምስክር የሆኑ አባት
ጊዜ ቲዩብ gize tube ጊዜ ቲዩብ gize tube
268K subscribers
197,658 views
6.4K

 Published On Aug 17, 2020

ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የቅዱሳን መናኸሪያ ናት። እልፍ ቅዱሳን የተጋድሎ በዓታቸው፣ የጸሎት ዋሻቸው አድርገው የጽድቃቸው መነሻም ሆነ ፍጻሜ አድርገዋታል። ራሱ ጌታችን በአካል እየተገለጠ ታላላቅ ምሥጢራትን የገለጠላቸው ብዙ ቅዱሳን አሉ፤ ክብርት እመቤታችንም እየተገለጠችላቸው ሰማያዊ ምሥጢር የነገረቻቸው እነ ቅዱስ ኤፍሬም፣ እነ አባ ሕርያቆስ፣ እነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣ እነ አባ ጽጌ ድንግል እና ሌሎችም በርካታ ቅዱሳን አሉ። ቅዱሳን መላእክት ሰማያዊ ኅብሥትና ጽዋ እያመጡላቸው ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ሲፈትተቱ የነበሩ አሉ፤ የተጋድሎአቸው ብርታት፣ የጸሎታቸው ኃይል የእምነታቸው ጽናት ለጽድቅ ያበቃቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ቅዱሳን ብቻ ከ900 በላይ ናቸው-ለዚያውም ገድል ተጽፎላቸው ጽላት ተቀርጾላቸው ቅድስናቸው የተመሰከረላቸው ናቸው እንጂ እግዚአብሔር ብቻ የሚያውቃቸው እልፍ ቅዱሳን አሏት ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ። ከእነዚህ መካከል ታዲያ ሞትን ሳይቀምሱ እንደነ ሄኖክም እንደነ ኤልያስም የተሰወሩ ብዙ ቅዱሳን አባቶችም መኖራቸው ይታወቃል የሚደንቀው ታዲያ አሁን አለም እንደዚህ ውጥንቅጡ ውስጥ ባለችበት ሰዐት ዛሬም ኢትዮጵያውያን የሆኑ ቅዱሳን አባቶች እና እናቶች እየተሰወሩ ሀይለ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ ሰፍፎ እንደሚገኝ ማሳያ እየሆኑ ነው ዛሬም ብዙ ቅዱሳን በዚህ ገዳም ይሰወራሉ መሰወር ብቻ አይደለም በጣም ብዙ የተሰወሩ ቅዱሳን አባቶች እንዳሉም በግልፅ ይታወቃል እንደገናም በገዳሙ የብርሀን ምሰሶ ተተክሎ ይታያል ገዳሙ ቅዱስ ዐራኤል ለመጨረሻ ግዜ የክርስቶስን የደሙን ፅዋ ያንጠፈጠፈበትም ቦታ ነው ይህ ቦታም ሲነሳ አብረው የሚነሱት እንደ ኢያሱ ፀሀይ ያቆሙት፣ እንደ ሙሴ ባህር የከፈሉት አባት ለዚህ ቦታ ቅድስና የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡

show more

Share/Embed