ገጣሚ፦እንግዳዬሁ ዘሪቱ ርዕስ፦ተስፋ የራቀ' ለት
የገጣሚያን ማህበር የገጣሚያን ማህበር
656 subscribers
5,894 views
59

 Published On Apr 29, 2024

ተስፋ የራቀን ለት'✍

የቀስተደመናትን : ፍንትው ብሎ መውጣት
ሽቅብ እየቃኘን : ሰለስቱን ቀለማት
የቃል ኪዳን ትውስታን : ውስጣችን አይጭርም
ከቀለም ያለፈ : ፍቺን አይሰጠንም።
.........................
ፍካትን ተላብሶ
ሃሴት አግበስብሶ
እንደበጋ ፀሐይ : የጠራው ሰማይም
ከመግጠጡ በቀር : ፍካት አያሳይም።
..........................
የቀኑን እሩጫ : የጨለማውን ሽሚያ
እየተከታተሉ : የምሽቱን ፍልሚያ
ተግተው በመታደም : ሌሊቱን ሳይፈሩ
ያውም በዜማቸው : ውጤት ያበሰሩ
የአዕዋፍቱ ፉጨት : ትርጉም አይሰጠንም
የሃሴትን ስሜት : ከቶ አያድለንም።
.............................

show more

Share/Embed