የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአየር ንብረት ለውጥ ፐርፎርማንስ ፕሮጀክት የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ የዘይትና ሩዝ ድጋፍ አደረገ
Ethiopian Ministry of Industry Ethiopian Ministry of Industry
1.13K subscribers
10 views
0

 Published On Apr 9, 2024

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኢድ አልፈጥር በአልን ምክንያት በማድረግ   በፕሮጀክት ሳይት አከባቢ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ አደረገ
====================
መጋቢት 30/2016 ዓ.ም (ኢ.ሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር የአየር ንብረት ለውጥ ፐርፎርማንስ ፕሮጀክት በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አሚባራ ወረዳና በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሽንሌ ወረዳ ለሚገኙ የፕሮጀክቱ የሳይት ሰራተኞቹና የአካባቢው የማህበረሰብ ክፍሎች የዘይትና ሩዝ ድጋፍ አድርጓል።

የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት አለሙ እንደገለፁት ድጋፉ በሁለቱም ፕሮጀክት ሳይቶች  600 ለሚደርሱ አባዎራዎች እና የሳይት ሰራተኞች የኢድአልፈጥርን በዓል ምክንያት በማድረግ የሩዝና የዘይት ድጋፍ እንደተደረገ ገልፀዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአርሶ አደሩን የእርሻ መሬት በመውረር  የአካባቢውን ስነ ምህዳር በማዛባት የህብረተሰቡ ኑሮ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደረ ያለውን ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ(ወያኔ ሀራ) መጤ አረም ዘመናዊ ማሽን በመጠቀም  ከአካባቢው በማፅዳት የእርሻ መሬቱን እንዲጠቀሙበት ከማድረጉም በላይ መጤ አረሙን ወደ ባዮማስ አማራጭ ሃይል በመቀየር ለስሚንቶ ፋብሪካዎች የድንጋይ ከሰልን በመተካት ጥቅም ላይ እንዲውል በማድረግ የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀትን ከመቀነስ ባሻገር ለድንጋይ ከሰል ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ማዳን የሚያስችል የቴክኖሎጂ ሽግግር  ስራ እየሰራ ስለመሆኑ ገልፀዋል።

አቶ ዳዊት አክለውም ድጋፉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከህብረተሰቡ ጎን መሆኑን ለመግለፅና እንኳን ለኢድአልፈጥር በዓል አደረሳችሁ ለማለት እንደሆነ በመግለፅ ድጋፉ በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚቀጥል ገልፀዋል ።

show more

Share/Embed