መክሊትን ማትረፍ! ገብርኄር ሥድስተኛ ሳምንት
አንቀጸ ብፁዓን አንቀጸ ብፁዓን
1.87K subscribers
135 views
15

 Published On Apr 14, 2024

🔴በአንቀጸ ብፁዓኝ ቲዩብ በቅርቡ አዲስ መዝሙር ይጠብቁ🔴

#amharicnews #ethiopia #aba_gebrekidan_interview
#mezmure #ethiopianews #sibket

ገብርኄር
ስድስተኛው ሳምንት ‹ገብር ኄር› የሚል ስያሜ አለው፡፡ ‹ገብርኄር› ማለት ‹በጎ፣ ታማኝ፣ቸር አገልጋይ› ማለት ነው፡፡ ስያሜው ከማቴዎስ ወንጌል ፳፭፥፲፬ የተወሰደ ሲኾን፣ ታሪኩም እግዚአብሔር በሰጠው ጸጋ በታማኝነት ማገልገል የሚያስገኘውን ዋጋ ያስረዳል፡፡ አንድ ሰው አገልጋዮቹን ጠርቶ ወጥተው፣ ወርደው፣ ነግደው እንዲያተርፉ ለአንዱ አምስት፤ ለአንዱ ሁለት፤ ለአንዱ ደግሞ አንድ መክሊት ሰጣቸው፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለው በተሰጠው መክሊት ነግዶ፣ ሌላ አምስት መክሊት አትርፎ፣ ዐሥር አድርጎ፣ ‹‹ጌታዬ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ ወጥቼ ወርጄ አምስት አትርፌአለሁ›› ብሎ ለጌታው አቀረበ፡፡ ጌታውም ‹‹አንተ ጎበዝ እና ታማኝ ባሪያ! በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ!›› አለው፡፡ ሁለት መክሊት የተቀበለውም ወጥቶ፣ ወርዶ፣ አትርፎ አራት አድርጎ አቀረበ፡፡ እርሱንም ጌታው ‹‹አንተ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃልና ወደ ጌታህ ደስታ ግባ!›› አለው፡፡ አንድ የተቀበለው ሰው ግን መክሊቱን ወስዶ ቀበራት፡፡ ጌታው በተቈጣጠረው ጊዜም የቀበራትን መክሊት አምጥቶ ‹‹አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ፣ ካልበተንህበት የምትሰበስብ ጨካኝ እንደ ኾንኽ ዐውቃለሁ፡፡ ስለዚህ ፈራሁና የሰጠኸኝን መክሊት ቀበርኳት፤እነሆ መክሊትህ!›› ብሎ ምንም ሳያተርፍ መክሊቱን ለጌታው መልሶ አስረከበ፡፡ ጌታውም ‹‹አንተ ክፉና ሐኬተኛ ባሪያ! ወርቄን በጊዜው አታስረክበኝም ነበር? ነግዶ ለሚያተርፍ እሰጠው ነበር፡፡ ይህን ክፉና ሐኬተኛ ባሪያ እጅ እግሩን አስራችሁ ጨለማና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ሥፍራ ውሰዱት! መክሊቱን ቀሙና ለባለ ዐሥሩ ጨምሩለት!›› ብሎ አዘዘ፡፡
በዚህ ታሪክ እንደምናየው በተሰጠው መክሊት ያተረፈ ሰው (ክርስቲያን) ዋጋ አለው፡፡ በፈጣሪው ዘንድ መልካም፣ በጎ፣ ታማኝ ባሪያ ተብሎ ይሸለማል፡፡ ባያተርፍ ደግሞ ሐኬተኛ ባሪያ (አገልጋይ) ይባላል፤ ቅጣቱንም ይቀበላል፡፡ እንግዲህ እኛም ታማኝ አገልጋይ መኾን ይጠበቅብናል፡፡ ሳምንቱ ይህ መልእክት የሚተላለፍበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ ዘመን በመክሊታቸው የሚያተርፉ እንዳሉ ዅሉ፣ መክሊታቸውን (ጸጋቸውን) ዝገት እስከሚያጠፋው ድረስ የሚቀብሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ መክሊትን (ጸጋን) መቅበር ዋጋ የማያሰጥ መኾኑን ተገንዝበን በቻልነው መጠን ለማትረፍ መትጋት እና ታማኝ አገልጋይ መኾን እንደሚገባን ከገብር ኄር ታሪክ እንማራለን፡፡

🔴SUBSCRIBE,SHARE,LIKE🔴

   • "ሊቅ ሰምተን ስለማናቅ ያለው ሰው ሊቅ ይመስለናል" #ርዕሰ...  
   • ርዕሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረ ኪዳን "ኹሉም ሰው በአንድ...  
   • በጅራፍ አስወጣቸው!  ሦስተኛ ሳምንት ዐቢይ ጾም! #aba_...  
   • ቅድስት የዐቢይ ጾም ኹለተኛ ሳምንት። ቅድስት ማለት ምን ማ...  

❗Follow us❗
   / @anketsebtsuan12  
  / anketse_btsuan_12  
የሕይወት ጹሑፍ👉 https://t.me/AneketseBtsuan12/42


#aba_gebrekidan_interview
#ethiopianews
#amharicnews
#eritreannews
#mezmure
#አባ_ገብረኪዳን_ግርማ
#አባ_ገብረኪዳን_ስብከት
#new
#news
#newsibket
#newsong
#newmovie
#newshorts
#abelbirhanu
#donkeytube
#comediameahetu
#ማንእንደሀገር
#newstandupcomedy
#ኮሜዲያን
#እሸቱመለሰ
#ማን_እንደሃገር
#ድንቅልጆች #21media #ጃንደረባው #eotc #mk #motivational

show more

Share/Embed