ሀገር ውስጥ የሚመረቱ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶችን በመጠቀም ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መተካትና የሀገራችንን ምርት በኩራት መጠቀም አለብን
Ethiopian Ministry of Industry Ethiopian Ministry of Industry
1.13K subscribers
20 views
0

 Published On Premiered Dec 26, 2022

ሀገር ውስጥ የሚመረቱ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶችን በመጠቀም ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መተካትና የሀገራችንን ምርት በኩራት መጠቀም አለብን (ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ)
-------------------------

ታህሳስ 17/2015ዓ.ም(ኢ.ሚ) የሀገራችን ኢኮኖሚ በማይናጋ መሰረት ላይ ለመጣል አምራች ኢንዱስትሪው የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን በመረዳት መንግስት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠቱ ኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ መጀመሩ ይታወቃል፡፡

ሀገራዊ ንቅናቄው ተዘግተው የነበሩ ኢንዱስትሪዎችን ወደ ስራ በመመለስ ረገድ ያመጣውን ለውጥ እና በጦርነት ምክንያት የተጎዱ ኢንዱስትሪዎችን ወደ ስራ መግባታቸውን በተመለከተ በኮምቦልቻ ከተማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ከፍተኛ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እኛው ሰርተን የሌሎችን ሀገራት ሎጎ ለጥፈን ወደ ውጭ በመላክ መልሰን የምንገዛበት ሂደት ለማቆምና ራሳችንን እንድንመረምር ኮምቦልቻ ያሉ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ማሳያ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ሀገር ውስጥ የሚመረቱ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶችን በመጠቀም ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መተካትና የሀገራችንን ምርት በኩራት መጠቀም አለብን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ዐብይ ሀገራችን አምራችና ወጣት የሰው ኃይል ያላት፣እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትና መሰረተ ልማት ከማነኛውም የዓለም ሀገር በዝቅተኛ ዋጋ የሚቀርብባት በመሆኑ ባለሀብቶች በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ቢሰማሩ በእጅጉ አትራፊ እንደሚሆን በመገንዘብ ዘርፉን በመቀላቀል ለሀገራችው የኢኮኖሚ እድገትና ለወገናቸው የኑሮ መሻሻል እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉም ሆነ ሌሎች ሀገራዊ እቅዶችና እሳቤዎች ስኬታማ የሚሆኑት ሰላም ሲረጋገጥ በመሆኑ ለሰላም መረጋገጥና ሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች ስኬት እውን መሆን እጅ መቀሰራችን አቁመን ኃላፊነት በመውሰድና እጅ ለእጅ ተያይዘን ሰላማችንን በማረጋገጥ ኢኮኖሚያችን ማሳደግ ይገባል ብለዋል፡፡

show more

Share/Embed