የሥራ ስንብት/የአገልግሎት ክፍያ የሚገባው ሠራተኛ How to calculate Severance payment የክፍያ መጠንና የታክስ ስሌት
Beko Tube Beko Tube
800 subscribers
8,451 views
237

 Published On May 2, 2024

የስንብት ክፍያ የሚገባው ሠራተኛ
የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ (60 የስራ ቀናት) እና የጡረታ አበል ለመቀበል ብቁ ካልሆነ (አስከብሮ)

ድርጅቱ በመክሰሩ /በሌላ ምክንያት ለዘለቄታው በመዘጋቱ የሥራ ውሉ ሲቋረጥ፤

ሠራተኛው ከሥራ ሲቀነስ(አንቀጽ 29)፣
የድርጅቱን ድርጅታዊ አቋም ወይም የሥራ እንቅስቃሴ ሥራ፣ ምርታማነት መቀነስና ምርታማነትን ለማሳደግ አድስ አሰራር/ቴክኖሎጂ (አንቀጽ 28/3)


በአሠሪ /በሥራ መሪ ወሲባዊ ጥቃት /ትንኮሳ የተፈፀመበት እንደሆነ ወይም ድርጊቱ በሌላ ሠራተኛ እንደተፈፀመ ሪፖርት ተደርጎለት አሠሪው ተገቢውን እርምጃ ባለመውሰዱ ሠራተኛው የሥራ ውሉን ካቋረጠ፤

አሠሪው በሠራተኛው ላይ ሰብአዊ ክብሩንና ሞራሉን የሚነካ ወይም በወንጀል ሕጉ መሠረት የሚያስቀጣ አድራጎት በመፈጸሙ የተነሣ ሠራተኛው የሥራ ውሉን ያቋረጠ እንደሆነ፤

አሠሪው ለሠራተኛው ደኅንነት ወይም ጤንነት የሚያሰጋ አደጋ እንዳይደርስ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት እርምጃ ባለመውሰዱ የተነሳ ሠራተኛው የስራ ውሉን ሲያቆርጥ፤
ሙሉ ወይም ዘላቂ የአካል ጉዳት በመድረሱ ሠራተኛው ሥራ ለመሥራት አለመቻሉ በሕክምና ተረጋግጦ የሥራ ውሉ ሲቋረጥ፤

ቢያንስ 5 ዓመት በአሠሪው ዘንድ የሥራ አገልግሎት ኖሮት በህመም ወይም በሞት የሥራ ውሉ ሲቋረጥ

ቢያንስ 5 ዓመት በአሠሪው ዘንድ የሥራ አገልግሎት ኖሮት በሥራው ላይ የሚያስቆይ ከሥልጠና ጋር የተያያዘ ለአሠሪው የውል ግዴታ ሳይኖርበት ሥራውን በገዛ ፈቃዱ ሲለቅ፤

በኤችአይቪ/በኤድስ ህመም ምክንያት በራሱ አነሳሽነት የሥራ ውሉን ያቋረጠ እንደሆነ

በሕግ ከተደነገገው ምክንያት ውጭ በአሠሪው አነሳሽነት (አንቀጽ28) የሥራ ውሉ ሲቋረጥ፤

በአሰሪው አነሳሽንት በማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ስለማቋረጥ (አንቀጽ28)
የሠራተኛው ችሎታው ቀንሶ ሲገኝ

ሠራተኛው በጤንነት መታወክ /በአካል ጉዳት ምክንያት ግዴታውን ለመፈጸም ለዘለቄታው የማይችል ሲሆን፤

ድርጅቱ ወደሌላ ቦታ ሲዛወር ሠራተኛው ወደአዲሱ ቦታ ተዛውሮ ለመሥራት ፈቃደኛ ካልሆነ፤

ሠራተኛው የያዘው የሥራ መደብ በበቂ ምክንያት ሲሰረዝና ሠራተኛውን ወደሌላ ሥራ ማዛወር የማይቻል ሲሆን፡፡

አሠሪው ምርቶች / አገልግሎቶች ተፈላጊነት መቀነስ ምክንያት የድርጅቱ የሥራ እንቅስቃሴ በመቀዝቀዙ ወይም ትርፍ እየቀነሰ በመሄዱ፤

የአሰራር ዘዴዎችን ለመለወጥ ወይም በአዲስ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ሲባል የሚደረግ የሥራ ውል መቋረጥ የሚያስከትል ውሣኔ፡፡

በአሰሪ አነሳሽነት ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ስለማቋረጥ (አንቀጽ27)
ሀ) ሠራተኛው የሥራ ሰዓት ባለማክበር፡- የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው በ6 ወር ውስጥ በጠቅላላው ለ8 ጊዜ የስራ ሰዓት ካላከበረ፤

ለ) በህግ ከተሰጡት እረፍቶችና ልዩ ልዩ ፈቃዶች ውጭ፡- የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው በ6 ወር ውስጥ ለ5 ቀናት ከስራ ከቀረ፤

ሐ) በሥራው ላይ የማታለል ተግባር ከፈፀመ፤

መ) የራሱን /የሌላ ሰው ብልጽግናን በመሻት የአሠሪውን ንብረት /ገንዘብ አለአግባብ ከተጠቀመ፤

ሠ) ሠራተኛው ሥራውን የመሥራት ችሎታ እያለው የሥራ ውጤቱ ባለማቋረጥ የምርት ጥራትና መጠን በታች ሲሆን፤

ረ) በሥራው ቦታ አምባጓሮ /ጠብ አጫሪነት ተጠያቂ ከሆነ፤

ሰ) በወንጀል ጥፋተኛ በመሆኑ ፤

ሸ) በአሠሪው ንብረት ላይ ሆነ ብሎ /በከባድ ቸልተኝነት ጉዳት ማድረስ፤

ቀ) በሠራተኛው ላይ ከ30 ቀናት ለሚበልጥ ጊዜ የእሥራት ፍርድ ተወስኖበት ከሥራ ሲቀር፤


የሥራ ውል ሲቋረጥ ደመወዝና ተያያዥ ክፍያዎችን ስለመክፈል
(አንቀጽ 36)
የሥራ ውል ሲቋረጥ የሠራተኛው ደመወዝና ከውሉ መቋረጥ ጋር የተያያዙ ክፍያዎች ሁሉ 7 የሥራ ቀናት ውስጥ መከፈል አለባቸው፡፡

የክፍያው ጊዜ ሊራዘም የሚችለው ሠራተኛው ከአሠሪው የተረከበውን ንብረት በማስረከብ ወይም የሚፈለግበትን ማናቸውም ሂሣብ በማወራረድ ረገድ በራሱ ጥፋት ያዘገየ እንደሆነ ነው፡፡

ሠራተኛው የጠየቀው ክፍያ አስመልክቶ አለመግባባት የተፈጠረ እንደሆነ አሠሪው በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ለሠራተኛው ያመነውን ያህል መክፈል ይኖርበታል፡፡ (አንቀጽ 37)

ከአሠሪው ቁጥጥር ውጭ በሆነ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር በ7 የስራ ቀናት ውስጥ አሠሪው ለሠራተኛው መክፈል የሚገባውን መጠን ካልከፈለ ክፍያው ለዘገየበት ጊዜ አሠሪው ለሠራተኛው እስከ 3ወር የሚደርስ ደመወዙን እንዲከፍል ሊወስን ይችላል፡፡(አንቀጽ 38)


የሥራ ስንብት የክፍያ መጠን
ለመጀመሪያው የአንድ ዓመት አገልግሎት የሠራተኛው የመጨረሻ ሣምንት አማካይ የቀን ደመወዙ በ30 ተባዝቶ ይከፈለዋል፡፡

ከአንድ ዓመት በታች ያገለገለ ሠራተኛ ግን እንደአገልግሎት ጊዜው እየተተመነ ተመጣጣኝ ክፍያ ያገኛል፡፡

ከአንድ ዓመት በላይ ያገለገለ ሠራተኛ ተጨማሪ ክፍያ ለእያንዳንዱ የአገልግሎት ዓመት የመጨረሻ ሣምንት አማካይ የቀን ደመወዙ 1/3 እየታከለ ይከፈለዋል፡፡

ጠቅላላው ክፍያ ከሠራተኛው የ12 ወራት ደመወዝ መብለጥ የለበትም፡፡ እና የታክስ ስሌት

Example
Employee Bereket
Hiring date Feb 15, 2013
Termination date April 20, 2020
Salary 30,000



Note12 months salary
30,000*12= 360,000



1st yr service 30,oo0
30,000*1/3*6=60,000
30,000*1/3*65/365=1,780.82
30,000+60,000+1,780.82
=91,780.82

Total severance = 91,780.82
Months (91,780.82/30,000) = 3.059360731 ~3.06months

For 1 month tax 30,000*0.35-1,500=9,000
For 3months tax 9,000*3=27,000
0.06 month salary 30,000*0.06=1,800
0.06 month tax 1,800*0.15-142.5=127.5

Total tax=27,000+127.5= 27,127.5
Net severance 91,780.82-27,127.5=64,653.32
Entry
severance pay………91,780.82
tax…………………………….……….27,127.5
cash………………………….………..64,653.32

Tax liab…………27,127.32
cash………………………..27,127.32

show more

Share/Embed