አልሀምዱሊላህ. ሸሂዶቹ የተረሱ መስሎን ነበር! seifu on ebs / minber tv// ethiopia
Hiba tube Hiba tube
116K subscribers
1,661 views
222

 Published On Aug 2, 2024

በስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ ለሸሂድ ወንድሞች የተቆፈረው ንፁህ የመጠጥ ውሃ ጉድጓድ ተመርቆ አገልገሎት መስጠት ጀመረ።

በሸገር ሲቲ የመስጅድ ፈረሳን በመቃወም በአንዋር መስጅድ በተካሄደ ተቃውሞ ህወታቸውን ላጡ ስድስት ሸሂድ ወንድሞች ስም የሰደቀተል ጃሪያ ሶስት የንፁህ መጠጥ ውሃ ጉድጓድ ተቆፍሮ ለአካባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ሂባ ፋውንዴሽን አሰታውቋል።

ሶስቱ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ጉድጓድ በሂባ ፋውንዴሽን እስላማዊ ድርጅት አሰተባባሪነት ከኢትዮ ሙስሊም መረዳጃ ማህበር በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በአልቾ ውሪሮ ወረዳ ስሎ ቀበሌ እና ለምለም 1ቀበሌዎች ለሚገኙ ነዋሪዎች የንፁህ መጠጥ ውሃ እንዲያገኙ ማድረግ እንደተቻለ የሂባ ፋውንዴሽን እስላማዊ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ወጣት ሙባረክ አደም ተናግረዋል ።
በሰደቀተል ጃሪያ በስማቸው ንፁህ የመጠጥ ውሃ ጉድጓድ የተቆፈረላቸው በሸሂድ ሲራጅ ማህሙድ፣ በሸሂድ አቡበከር ኤሊያስ፣ በሸሂድ ኢብራሂም ደምበል፣ በሸሂድ ዙበይር ሙደሲር፣ በሸሂድ ጀሚል ሪድዋን እና በሸሂድ አንዋር ሱሩር ስም እንደሆነ ወጣት ሙባረክ ገልፀዋል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮ ሙስሊም መረዳጃ ማህበር ቁ 2 አባላት የሸሂድ ወንድሞቻችን ቤተሰቦች የአልቾ ውሪሮ ወረዳ የተለያዩ የመንግስት አካላት በተገኙበት ተከናውኗል።

በምረቃው ስነ ስርአት ላይ ንግግር ያደረጉ የሸሂድ ቤተሰቦች የውሃ ጉድጓዱ በሸሂዶች ስም መቆፈር እጅግ በጣም እንዳስደሳታቸው ገልፀው፤ ሸሂዶቹ የተረሱ መስሎን ነበር የሚያስታውሳቸው አካል ማግኘታችን በእጅጉ አስደስቶናል ሲሉ ገልፀዋል።
ለፕሮጀክቱ መሳካት የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉትን የኢትዮ ሙስሊም መረዳጃ ማህበር አባላት እና የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች የሸሂድ ቤተሰቦች ምስጋና አቅርበዋል ።

ሂባ ፋውንዴሽን እስላማዊ ድርጅት በሰደቀተል ጃሪያ ለቤተሰባቸው የንፁህ የመጠጥ ውሃ ማስቆፈር ለሚፈልጉ ድርጅቱ ማንኛውንም በጎ ሰራ ለማስተባበር ሀላፊነት ወስዶ ለማስራትና በተፈለገው ሰዐት ለማስረከብ ሙሉ ዝግጁ መሆኑነን ወጣት ሙባረክ ተናግረዋል

በሀገራችን ኢትዮጵያ በገጠሩ ለሚኖሩ የውሀ ችግር ላለባቸው ወገኖች ከተለያዩ ድርጅቶችና አኽለል ኸይሮች ጋር በመተባበር ከ68 በላይ ንፁህ የውሀ ጉድጓድ ማስቆፈሩንና በሺዎች ለሚቆጠሩ አባወራዎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ስራዎች ስርቶ ማሰረከብ መቻሉን አሳውቀዋል።
በሂባ ፋውንዴሽን የሚሰሩ በጎ ስራዎች በተለይም በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍል ለሚገኙ እና የአክፍሮት ኃይላት አደጋ የተጋረጠባቸውን የማህበረሰባችን ክፍል ለመታደግ በሚሰሩ የመስጂድ ፣የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ እና የቁርዓን ስርጭት በተጨማሪም በገጠር ለሚገኙ አኡስታዞችና ኢማሞች ደሞዝ ለመክፈል በምናደርገው ጥረት ከጎናችን እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን።. Hiba Foundation Islamic Organization
1000597724563 Commercial bank
7943867089911 Dashen bank
1000050540001 Hijra bank
0035690010301 Zamzam bank
8800000766882 Amhara bank
1000094919642 CBO
168180888 Abysinia bank
ስልክ 0937060707
0921125054
telegram : https://t.me/hibafoundation
whatsapp: https://chat.whatsapp.com/KrdTVxwTvz2...
facebook : facebook.com/hibafoundationislamicorg
email : [email protected]
ቤተል ቢጫ ፎቅ ፊት ለፊት MK ህንፃ 1ኛ ፎቅ

show more

Share/Embed